+251- 114 43 14 44 [email protected]

ታምሪን ሞተርስ አዲስ ያስመጣዉን ሱዙኪ ኢኮ ቫን ሞዴል በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ

ለአካባቢ ሥነ ምህዳር ምቹ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ከሚያመርተው እና በዓለም ታዋቂ ከሆነው የሱዙኪ ኩባንያ ጋር ህጋዊ አከፋፋይ በመሆን የሚሰራው ታምሪን ሞተርስ፣ በዓይነትና አማራጨ በርካታ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ ከጀመረ ዓመታትን ተሻግሯል፡፡

ታምሪን ከሱዙኪ ሞተርስ ኩባንያ ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ተከትሎ እስከ ዛሬ ድረስ ከ10 በላይ የተለያዩ አውቶሞቢሎችን እንዲሁም የጥገና፣ የወቅታዊ ሰርቪስ እና የስፔርፓርት አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በማቅረቡ ስኬታማ ለመሆን በቅቷል፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመራጭነታቸው ጎልቶ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ከሚሽከረከሩት የተለያዩ ሞዴል የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች አቅርቦት ጀርባ ታምሪን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

ወቅትን የጠበቀ ጥገና እንዲሁም ተፈላጊውን የመኪና ግብዓት ለአውቶሞቢሎች ማሟላትን የሚያዉቅበት ታምሪን ሞተርስ፣ ለደንበኞቹ አስፈላጊ የሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በበቂ መጠን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረቡም ባሻገር ለደንበኞች ይበልጥ ለመቅረብ በኢትዮጲያ አውቶሞቲቭ ኢንደስትሪ አዲስ አሰራርን በመዘርጋት ደንበኞች ያሉበት ቦታ ሆነው የመደበኛ አገልግሎት የሚያገኙበትን ተንቀሳቃሽ ወርክሾፕን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የተንቀሳቃሽ ወርክሾፕ አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።

ታምሪን ሞተርስ ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚያስገባቸው ተሽከርካሪዎች በተጫማሪ በሀምሌ 29 2015 በሱዙኪ ሞተር ኮርፖሬሽን በኩል የንግድ ስራን ለማገዝ አልሞ ለገበያ ያቀረበውን ሱዚኪ ኢኮ ቫን ተሽከርካሪን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ተጋባዥ ደንበኞች እና እንግዶች በተገኙበት የማስተዋወቅ ስነ ስርዓት ፈጽማል።

አዲሱን ሞዴል ለማስተዋውቅ በነበረው ስነ-ስርዓት ላይ የተጋበዙት ወ/ሮ የምንጭ ወርቅ ፍቃዱ ከታምሪን ሞተርስ ሱዙኪ ሴላሪዮ ሞዴል መኪናን ከዚህ በፊት ገዝተዋል፡፡ ወ/ሮ የምንጭ ወርቅ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ብዙም የመኪና እዉቀት አልነበረቸዉም፡፡ መኪና ለመግዛት ሲያስቡ በርከታ አማራጮች አንደነበራቸዉ አዉስተዉ፤ ከቀረቡላቸዉ አማራጮች ታምሪን ሞተርስን ምርጫቸዉ አድርገዋል፡፡ ምክንያታቸዉ ደግሞ ግልፅና ቀልጣፋ አሰራርን መከተላቸዉ ነዉ፡፡ ወደ ታምሪን ሞተርስ ሲመጡ ባገኙት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡ የተመኟትን ሱዙኪ ሴላሪዮ ሞዴል መኪናን የግላቸዉ አድርገዋል፡፡ ወ/ሮ የምንጭ ወርቅ ከአባይ ባንክ ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት 50 በመቶዉን የመኪናዉን ዋጋ ከፍለዉ ቀሪዉን ደግሞ በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር የመኪና ባለቤት ሆነዋል፡፡ ታምሪን ሞተርስ ለሰጣቸዉ የተቀላጠፈ አገልግሎት አመስግነዋል፡፡ የገዙት ሱዙኪ ሴላሪዮ ሞዴል መኪና ነዳጅ ቆጣቢ በመሆኑና የሶስት አመት ዋስትና በማግኘታቸዉ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደመምታት ነዉ የማየዉ ብለዋል፡፡

አቶ ተስፋዮ ሌላኛዉ የታምሪን ሞተርስ ደንበኛ ናቸዉ፡፡ በገዙት የሱዙኪ ግራንድ ቪታራ መኪና ደስተኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ከታምሪን ሞተርስ ባገኙት አገልግሎት ግንኙነታቸዉ ከደንበኝነት ተሻግረዉ ቤተሰባዊ ሆኗል፡፡ መኪናዉም 5ሽህ ኪ.ሜ ሲሞላ የሰርቪስ አገልግሎት እንደሚሰጡት ገልፀዋል፡፡ ምንም አይነት መረጃ ሲፈልጉም ሰራተኞቹ በቀናነት ያስተናግዱኛል ብለዋል፡፡ ሌሎችም ታምሪን ሞተርስን ምርጫቸዉ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡

ሱዙኪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማና ተፈላጊ ከሆኑ የመኪና አምራቾች አንዱ ሲሆን፣ ዘመኑን የዋጁ የቤት አውቶሞቢሎችና እቃ ጫኝ መኪኖችን ለዓለም አቀፍ ገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡ የጃፓኑ ኩባንያ በተለያዩ ሃገራት የሚፈበርካቸው መኪኖች ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ሚሊዮን ደንበኞች የሚገለገሉባቸው፣ ጥራትን ከዋጋ፣ ምቾትን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ መሆናቸው ይበልጥ ተመራጭ እንዳደረጋቸዉ በርካታ ፁሁፎች አትተዋል፡፡

ታምሪን ሞተርስ የሚያስመጣቸዉ ተሸከርካሪዎች ለአካባቢ ሥነ ምህዳር ምቹ የሆኑ ናቸዉ፡፡ ድርጅቱ የተሰማራባቸውን ዘርፎች ዘመናዊ በሆነ የቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲመራ፣የደንበኞች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ምርቶችን እንዲቀርቡ እየተጋ ነዉ፡፡

በታምሪን ሞተርስ የሽያጭ ኦፊሰር የሆነችዉ ወ/ሪት ፍሬህይወት ሀይሌ ድርጅታቸዉ ከሱዙኪ ሞተርስ ኩባንያ ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ተፈላጊ የሆኑ መኪኖችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች እያቀረበ መሆኑን አዉስታለች፡፡

ድርጅታቸዉ በዓይነትና አማራጨ በርካታ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ ከጀመረ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል ብላለች፡፡ ታምሪን የደንበኞቹን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ለገበያ የሚያቀርባቸው የሱዙኪ መኪኖች ቁጥራቸዉ አስራ አንድ መሻገራቸዉን ነዉ የገለፀችዉ፡፡ እነዚህም አልቶ፤ ኤስ ፕሬሶ ፤ ሴላሪዮ፤ ዲዛይር፤ ስዊፍት ፣ ባሌኖ፤ ሲያዝ፤ ኤርቲጋ፣ ቪታራና ሱፐር ኬሪ ናቸዉ፡፡

ታምሪን ለውድ ደንበኞቹ አስፈላጊ የሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በበቂ መጠን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ለደንበኞች ማቅረቡን ነዉ ወ/ሪት ፍሬህይወት የተናገረችዉ፡፡ በተጨማሪም ታምሪን ሞተርስን ምርጫቸዉ አድርገዉ የተሸከርካሪ ግብይት ለሚፈፅሙ የ100,000KM ወይም የሶስት አመት ዋስትና እንደሚሰጥ ነዉ ያረጋገጠችዉ፡፡ ደንበኞችም ያሻቸዉን ተሽከርካሪ ከመገናኛ ወደ ኢምፔሪል ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት እንዲሁም ከሃያት ሆስፒታል ወደ ቦሌ መድሃኔአለም ቤተክርስትያን በሚወስደው መንገድ ዘ ሃብ ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው ሽያጭ ክፍል በመምጣት መመልከትና ግብይት መፈፀም ይችላሉ ብላለች፡፡

ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ አሰራር እየተገነባ ያለው የሱዙኪ መኪኖች ማሳያ (ሾውሩም) ሁሉንም ዓይነት ሞዴል መኪኖችን በአንድ አዳራሻ ማሳየት የሚችል ሲሆን፣ ይህም ማለት በአንድ ጊዜ በርካታ የተለያዩ ሞዴል የሱዙኪ መኪኖችን ለእይታ ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡

የታምሪን ሞተርስ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እያሱ ገበየዉ ከመለዋወጫ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከበቂ በላይ በሚባል ደረጃ የመለዋወጫ ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ይገኛል ብለዋል፡፡ ድርጅታቸን የድህረ ሽያጭ፣ የጥገና አገልግሎቶች እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ፈጣን ሰርቪስ  አገልግሎት ይሰጣል ነዉ ያሉት፡፡ እንደ ምክትል ስራ አስኪያጁ ገለፃ የአውቶሞቢል ተንቀሳቃሽ ፈጣን ሰርቪስ  አገልግሎት በታምሪን ሞተርስ ከሚሰጡ የድህረ ሽያጭ አገልግሎቶች አንዱ ሲሆን፣ ደንበኞች በእጅ ስልካቸው ደውለው ባሉበት አካባቢ የጥገና አገልግሎት የሚያገኙበት ነው፡፡

የሱዙኪ መኪናዎች ከሌሎች መኪኖች የተለየ ከሚያደርጋቸው አማራጮች ውስጥ ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የጃፓን መኪኖች መሆናቸው ሲሆን፣ ከዚህ ባሻገር በአገልግሎት ወቅት የሚጠይቁት ወጪ ዝቅተኛነቱ ሌላው የሚነሳ ልዩ መገለጫቸው ነው፡፡ ከጥገና አኳያ እነዚህ መኪኖች መደበኛ ሰርቪሳቸው ርካሽ የሚባል ሲሆን፣ የሚቀየሩ ወይም የሚተኩ የመኪና አካሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ይቻላል፡፡

የሱዙኪ አውቶሞቢሎች ስሪት ለኢትዮጵያ መልክዓምድር የተስማማ ሲሆን፣ በታምሪን በኩል ለኢትዮጵያ እየገቡ ያሉት ተሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ አየር ንብረት፣ የነዳጅ ጥራት ደረጃ እንዲሁም የባህር ጠለል ከፍታ እንዲስማማ ተደርጎ በልዩ ዲዛይን የተሰራ ነው፡ ፡በጠቅላላው የሱዙኪ መኪኖች ቀላል (ኮምፓክት) ፣ ለፓርኪንግ አመቺ፣ ነዳጅ ቆጣቢ መሆናቸው ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡  

ታምሪን ሞተርስ ሱዙኪ ከሚያመርታቸዉ መኪኖች አንዷ የሆነችዉን ሱዙኪ ኢኮ የ2023 አዲስ ሞዴል፣ እቃ ጫኝ መኪና በአስራ አንደኛ የሱዙኪ ሞዴልነት ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት አስተዋዉቋል፡፡ መኪናው በሱዙኪ ከ 2010 ጀምሮ እየተመረት የቆየ እንዲሁም በአለማቀፍ ገበያ ከአንድ ሚልየን በላይ ሞዴሎች በመሸጥ አገልግሎቱን እያስመሰከረ የቆየ ነው። ይሄ መኪና በዝናብም በፀሀይም የተጫነዉ እቃ እንዳይበላሽ ሽፍን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አንድ ነጥብ ሁለት ሊትር የሞተር ጉልበትና ሰባት ኩንታል የመጫን አቅም አለዉ፡፡ በሊትር እስከ 20 ኪ.ሜትር ድረስ የሚጓዘዉ ይህ መኪና ባለ አምስት ማርሽ ማንዋል ትራንስሚሽን ነዉ፡፡ ለደንበኞችም ወደ ሽያጭ ማእከሉ በመምጣት ድርጅቱ አዲስ ያስመጣዉን ሱዙኪ ኢኮ የስራ መኪና በመግዛት ስራዎን እንዲያሻሽሉ ጋብዘንዎታል፡፡

7 Comments

  1. Nebil

    የኢኮ ቫኑ ዋጋው ምን ያክል ነው።በባንክስ ይመቻችልኛል እኔ ያለኝ ብር አራት መቶ ሺህ ብር ብቻ ነው።

    Reply
    • Abdi Mohammed

      Do you have credit option???

      Reply
    • Mawcha Desta

      current price for Eeco van 2023

      Reply
  2. wendwesen regasa

    Good to hear that. can you tell the current price of suzuki eeco car. and please your tell.

    Reply
  3. መሳይ ይፋት

    suzuki scalerio መግዛት እፈልጋለሁኝ የኢትዮፕያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ ነኝ ስለዚህ የግዚ ብድር ፕሮሰስ ጨረሼ ብመጣ ዛሬ ላይ ዋጋው ስንት ነው

    Reply
  4. Sayat

    I was looking for suzuki every car or suzuki ecco van so can you tell the price please

    Reply

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

Spresso Recall

Spresso Recall

ክቡራን ደንበኞቻችንታምሪን ሞተርስ በኢትዮጵያ ውስጥ የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ወኪል አከፋፋይ ድርጅት በመሆን የሚታወቅ ኩባንያ ነው። በቅርቡ በተወሰኑ የ...

read more